Interrupt

ዲጂታል ኮምፒውተሮች ውስጥ፣ ኢንተራፕት ማለት ከሶፍትዌሩ ትኩረት የሚፈልግ ክስተት በሚኖርበት ወቅት ፕሮሰሰሩ የሚሰጠው ምላሽ ነው። የኢንተራፕት ሁነት ፕሮሰሰሩ በማሳወቅ፣ ሲፈቀድለት አሁን ላይ እየሰራ ያለን ኮድ ፕሮሰሰሩ እንዲያቋርጥ በማድረግ፣ ሁነቱ ጊዜውን በጠበቀ መልኩ እንዲከናወን ያደርጋል። ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ፣ ፕሮሰሰሩ የአሁን ላይ ስራዎቹን በማስቆም መልስ ይሰጣል፣ ስቴቱን ያስቀምጣል፣ እና ኢንተራፕት ሃንድለር (ወይም የኢንተራፕት ሰርቪስ ሩቲን፣ አይ.ኤስ.አር (ISR) የሚል መተግበሪያን በመጠቀም ለሁነቱ ምላሽ ይሰጣል። ይህ መስተጓጎል ጊዜያዊ ነው፣ እናም ኢንተራፕቱ ከባድ ችግር እስካልጠቆመ ድረስ፣ ፕሮሰሰሩ መደበኛ ስራውን ይቀጥላል ኢንተራፕት ሃንድለሩ ሲጨርስ። ኢንተራፕቶች በመደበኛነት በሃርድዌር መገልገያዎች ጥቅም ላይ የሚውሉ ሲሆን የኤሌክትሮኒክ ወይም የአካላዊ ሁነት ለውጦች ትኩረት እንደሚያስፈልጋቸው ለመጠቆም ጥቅም ላይ ይውላሉ። በተጨማሪም ኢንተራፕቶች ኮፕፒውተር ብዙ ስራ በሚሰራበት ጊዜ፣ በተለይ በሪል ታይም የኮምፒውቲንግ ስራ ጊዜ ለመተግበር ነው። ኢንተራፕትን በእዚህ መልኩ የሚተገብሩ ሲስተሞች ኢንተራፕት-መራሽ ይባላሉ።


From Wikipedia, the free encyclopedia · View on Wikipedia

Developed by Nelliwinne